Sales and Marketing, Promotion Jobs in Addis Ababa
Job Overview
አያት አክስዮን ማህበር በሪል እስቴት ልማት ላይ የተሰማራ አንጋፋ ድርጅት ሲሆን ከዚህ በታች በተገለጸው የስራ መደብ ውስጥ አመላካቾች አወዳድሮ በቋሚነት ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡
- የሥራ መደብ መጠሪያ፡ የገበያና ሽያጭ መምሪያ ስራ አስኪያጅ
- የትምህርት ዓይነት/ሙያ
- በማርኬቲንግ እና ሴልስ ማኔጀምንት የትምህርት ዘርፍ ከታወቀ ዩኒቨርሲቲ በባችለር ድግሪ የተመረቀ/ች እና8 ዓመት የሰራ/ች ከዚህ ውስጥ ቢያንስ 5 ዓመት በኃላፊነት የሠራ/ች ወይም
- በተመሳሳይ የትምህርት ዘርፍ በማስተርስ ድግሪ የተመረቀ/ች እና 7 ዓመት የሠራ/ች ከዚህ ውስጥ ቢያንስ 4 አመት በኃላፊነት የሠራ/ች
- የሥራ መደብ መጠሪያ፡ ከፍተኛ የገበያ ጥናት ባለሙያ
- የትምህርት ዓይነት/ሙያ
- በማርኬቲንግ እና ሴልስ ማኔጀምንት የትምህርት ዘርፍ ከታወቀ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ድግሪ የተመረቀ/ች እና በሙያው 4 ዓመት የሰራ/ች ወይም
- በተመሳሳይ የትምህርት ዘርፍ በማስተርስ ድግሪ የተመረቀ/ች እና በሙያው 3 አመት የሠራ/ች
- ልዩ ስልጠና፡ ኮምፒውተር ችሎታ ያለው/ት
- የሥራ መደብ መጠሪያ፡ ከፍተኛ የፕሮሞሽን ባለሙያ
- የትምህርት ዓይነት/ሙያ
- በማርኬቲንግ እና ሴልስ ማኔጀምንት የትምህርት ዘርፍ ከታወቀ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ድግሪ የተመረቀ/ች እና በሙያው 4 ዓመት የሰራ/ች ወይም
- በተመሳሳይ የትምህርት ዘርፍ በማስተርስ ድግሪ የተመረቀ/ች እና በሙያው 3 አመት የሠራ/ች
- ልዩ ስልጠና ፡ ኮምፒውተር ችሎታ ያለው/ት
ለሁሉም የስራ መደቦች
- ደመወዝ – በስምምነት ሆኖ ማራኪ
- የሥራ ቦታ- በዋናው መ/ቤት አዲስ አበባ
- ጾታ – አይለይም
- በሪል እስቴት ልማት ዘርፍ ላይ በተሰማሩ ድርጅቶች ውስጥ የሰሩና ልምድ ያላቸው አመልካቾች ይበረታታሉ፡፡
- ለተራ ቁጥር 2 እና 3- የስራ መደብ አክስዮን ማህበሩ የብር 1000 የትራንስፖርት አበልና በሽያጭ መጠን ላይ የተመሰረተ የኮሚሽን ፈጽማል፡፡