View more
2 months ago
ሲኒየር ፋይናንስ ኦፊሰር (አካውንታንት)
Job Overview
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስራ የሚገኘው የያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት “support to the Yared School of Music” በሚሰኝ ፕሮጀክት ከአውሮፓ ኀብረት የገንዘብ ድጋፍ ማግኘቱ የሚታወቅ ሲሆን፣ ይህንን የፕሮጀክቱን ሂሳብ በአግባቡ ለማንቀሳቀስ ከዚህ በታች ባለው ክፍት የስራ መደብ አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡
- የስራ መደብ መጠሪያ ፡ ሲኒየር ፋይናንስ ኦፊሰር (አካውንታንት)
- ደመወዝ ፡ 6300.00
- ብዛት፡ 1
- የስራ ቦታ፡ ያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት
- የቅጥር ሁኔታ፡ ለ8 ወር እና እየታየ የሚታደስ ለአንድ ዓመት
- ተፈላጊ ችሎታ፡
- ከኮሌጁ በሦስት ዓመት ትምህርት የተገኘ ዲፕሎማ ወይም በሌቭል 3 በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ ወይም በሂሳብ መዝገብ አያያዝ ተመረቀ/ች እና ከሥራው ጋር በቀጥታ የተያያዘ አግባብ ያለው የ3 ዓመትና ከዚያ በላይ የስራ ልምድ
- ከዚህ በፊት በመንግስት መ/ቤት ወይም መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት/የግል ድርጅት የተሰራበት የስራ ልምድ በወቅቱ የስራ ግብርን የከፈለበት ስለመሆኑ የተሰጠ የተሟላ ማስረጃ መያያዝ ይኖርበታል፡፡
ተጨማሪ ክህሎት
- ከዚህ በፊት ከEDF (European Development Found) ፐሮሲጀር ጋር ትውውቅ ያለው ወይም የስራ ቢሆን ይመረጣል፡፡
- በእንግሊዘኛና በአማርኛ ጥሩ የሆነ የንግግር እና የጽሁፍ ችሎታ ያለው፡፡
- መሠረታዊ የሆነ የኮምፒውተር ችሎታ ያለው እና የፒችትሪ ሶፍትዌር አጠቃቀም ስልጠና የወሰደ፡፡